አብዱ ኪያር : ደስ ይላል ABDU KIAR : Des Yilal New Ethiopian Music

Posted by on in Music

Details

ስጠብቅሽ ኖሬ ኖሬ ስናፍቅሽ ኖሬ ኖሬ
እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል ስለተገናኘን ዛሬ
ታጋሽ ሆኖ በመገኘት ቃል አክብሮ በመገኘት
እንዴት እኮ ደስ እንደሚል ተለያይቶ መገናኘት
የሩቅ ለሩቅ ፍቅር ያ ማይቻል ነገር

ብታምኝም ባታምኝም ወፈፍ አርጎኝ ነበር

መደንዘዝ አብዝቼ ከሰው አልጣጣም

ይቺን ዕለት ነበረ ምናፍቃት በጣም

በይ አይን አይንሽን ልየው አትለይ ከጎኔ

ዛሬ ነው ቀናችን ፍቅር አንቺና እኔ

ታግሶ ለቆየ ድሉ እራሱ ይደላል

የተለያየ ሰው ሲገናኝ ደስ ይላል

ደስ ይላል ደስ ይላል እንኳን ባይኔ አየሁሽ

ላመታት ናፍቄ ባካል አገኘሁሽ

ደስ ይላል ደስ ይላል ዛሬ ተገናኘን

እንኳንም አልቀረን እንደተለያየን

ደስ ይላል

ደስ ይላል

ደስ ይላል

ደስ ይላል

ስጠብቅሽ ኖሬ ኖሬ ስናፍቅሽ ኖሬ ኖሬ

እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል ስለተገናኘን ዛሬ

ታጋሽ ሆኖ በመገኘት ቃል አክብሮ በመገኘት

እንዴት እኮ ደስ እንደሚል ተለያይቶ መገናኘት

ያንን ሁሉ ዘመን ያንን ሁሉ ማታ

እንደ እብድ ሆኜ ነበር ባንቺ ሃሳብ ትዝታ

በማያልቀው ፍቅርሽ ስጎዳ ስቸገር

እንኳን አለፈ እንጂ ኑሮስ ከባድ ነበር

በይ አይን አይንሽን ልየው አትለይ ከጎኔ

ዛሬ ነው ቀናችን ፍቅር አንቺና እኔ

ቃሉን ላከበረ ፍቅር ብዙ ይከፍላል

የተለያየ ሰው ሲገናኝ ደስ ይላል

ደስ ይላል ደስ ይላል እንኳን ባይኔ አየሁሽ

ላመታት ናፍቄ ባካል አገኘሁሽ

ደስ ይላል ደስ ይላል ዛሬ ተገናኘን

እንኳንም አልቀረን እንደተለያየን

ደስ ይላል

ደስ ይላል

ደስ ይላል

ደስ ይላል

ደስ ይላል

እንዴት ደስ ይላል እንዴት ደስ ይላል

ተለያይቶ መገናኘት እንዴት ደስ ይላል::